በዘር ጭካኔ የተገደሉ ወገኖች ስታሳየኝ እኔ አረንጓዴ ማሳ አሳይሃለሁ የሰማንያ አራት አመት የታሪክ ምሁር እጁ በብረት ታስሮ ብታሳየኝ እኔ የትምህርት ቤት ምረቃ በአል አሳይሃለሁ I See No Evil, I Hear No Evil


አሻግረን አሻግረን እያላችሁ አትወትውቱኝ እስኪ እኔ ከተሻገርኩ በኋላ ድልድዩ ተሰብሯል ከአምስት አመት በኋላ እንደገና እሞክርላችኋለሁ


ጥያቄዎቹ ከቀናት በፊት ተሰጥተውኝ በደንብ ተዘጋጅቼበት ስለነበር እኮ ነው እንደዚህ ሁሉንም ሰው የሚያረኩ መልሶች መስጠት የቻልኩት በራሴ በጣም ኮርቻለሁ አይኔ ቢጉረጠረጥም በውስጤ ንዴት አልነበረም የማሳመን ችሎታዬ እየጨመረ የመጣ ይመስለኛል


ጨካኝ ነህ የምትሉኝ ለምን እንደሆነ አይገባኝም በየቀኑ ፈገግ እያልኩ አይደል? እናቴ ንጉስ ትሆናለህ ስላለችኝ በዛ መንገዴ ላይ ጥቂት ሺዎች ቢሞቱ፣ ሀገሪቱ ብትከፋፈል እኔ ምን ግድ ይለኛል።


ውሸት ታበዛለህ የሚሉኝም አሉ። እውነት እውነቱን እየመረጡ ቢሰሙኝ እኮ ችግሩ ይቀረፋል። በዛ ላይ ስዋሽ ፈገግ ለማለት እሞክራለሁ።


I See No Evil, I hear No Evil b/c i am one.


ሌላው ደሞ ስልጣኑን በጣም ይወዳል የሚሉኝ ነገር አለ። አዎ እወዳለሁ። ጠላ በስኳርም እንደዛው። የእናቴ ቃል ይፈጸም ዘንድ ትንሽ political chicanery ብጠቀም ይገርማል? After all, i See No Evil, I Hear No Evil


Top